የአቶ ለማ ጉያ ዜና እረፍት የውርስና ቅርስ ማህበረሰብ ቦርድ እንዳሳዘነው ገለጸ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ቦርድ፤ ሕዳር ሰባት ቀን ባደረገው የቦርድ ልዩ ስብሰባ ላይ የአቶ ለማ ጉያን ዜና እረፍት ተወያይቶ በእረፍታቸው ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን ገልጽዋል። በማስከተልም ለቤተሰቦቻቸው፤ ለዘመድና ወዳጆቻችው ፈጣሪ ለዚህ አሳዛኝ ጊዜ ብርታቱን እንዲሰጣችው ተመኝቱዋል።
ታዋቂ ሥራዎቻችውን ለማስታዎስ ያሀል እነዚህን የመልከቱ፤

የመቶ ሃያ አምስተኛውን (125ኛ) የአድዋ ድል በዓል በተለየ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት ጀምረናል።

የ125ኛው የአድዋ ድል በዓልን እጅግ በደመቀና ባመረ፤ ከበፊቶቹ ዝግጅቶቻችን ሁሉ በላቀ ሁኔታ ለማክበር አቅደን የነበረ ቢሆንም፤ በኮቪድ 19 ወረረሽኝ ምክያት በአዳራሽ ውስጥ ዝግጅቶቻችንን ማካሄድ እንደማይቻል ስለተገለጸልን በእጅጉ አዝነናል። ሆኖም ቴክኖሎጅ በፈቀደው መንገድ በርቀት (virtually) ተሳትፎ ለማካሄድ ዝግጅቶችን ጀምረናል። ስለአከባበራችንና ታዳሚዎች ስለሚሳተፉበት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ በዚህ ድረገጻችንና በሌሎች ዜና ማሳራጫዎች ላይ በቅርቡ እናሳውቃለን። ጥያቄ ካላችሁ ለድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለሆኑት ለአቶ ለይኩን ካሣሁን በኢሜል PR@EHSNA.Org በስልክ 717፟፟፟-574፟-1183 ወይም ለድርጅቱ ፕሬዝዳንት ለአቶ ተስፋዬ አምበርብር president@EHSNA.org ወይም በስልክ 703-718-6809 ማግኘት ይችላሉ።

ከሰላምታ ጋር

ተስፋዬ አምበርብር
ፕሬዘዳንት

የመቶ ሃያ አምስተኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለየ ሁኔታ እንደሚከበር መሀበሩ ዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ።

የ125ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በአማራጭ ዜና ማሰራጫ ሊከበር ነው። ለዚህ ዝግጅት ጽሁፍ አቅራቢዎችን ለመጋበዝ የመሀበሩ ቦርድ አባላት ዝግጅት ላይ መሆናቸውም ይገመታል። ይህ ታላቅ የጥቁር ሕዝቦች ድል በወቅቱ የኮሮና ተስቦ በሽታ ምክንያት እንደታሰበው በከፍተኛ ሁኔታ በምልዓተ ሕዝብ ማክበር ባይቻልም፤ በአማራጭ ዜና አገልግሎት በዓሉን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን የመሀበሩ አመራር አባላት እየተነጋገሩበት መሆኑም ታውቁዋል።

በአገራችን በዘርና በሀይማኖት ላይ ያተኮረና የሕዝብ ውርስና ቅርስ ላይ የደረስውን ጥፋት በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

EHSNA press release 9-19-2020

ETHIOPIAN HERITAGE
SOCIETY IN NORTH AMERICA
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ
1317 Orren Street NE, Washington, DC 20002
president@ehsna.org
pr@ehsna.org
703-718-6809
መስከረም 9 ቀን 2013 ዓ.ም.
(September 19, 2020)

ጉዳዩ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አየተፈጸመ ስላለው ጀኖሳይድና የንብረት ውድመት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈለግለት ስለማሳሰብ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ (ኢ.ው.ቅ.ማ.ሰ.አ.) ጥር 2003 ዓ.ም. ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የቀደሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ያወረሱንን ታሪክ፣ ትውፊትና ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍና ተተኪው ትውልድ በአገራችን ባሕልና ወግ እንዲታነጽ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷና አንድነቷ የተጠበቀ አንዲሁም ዜጎቿ በሰላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን የኢ.ው.ቅ.ማ.ሰ.አ. ጽኑ ምኞት አለው። ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ውስጥ ግምባር ቀደም የሆነውን የአድዋ ድል በማስመልከት የታሪክ ምሁራንን፣ ተመራማሪዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በመጋበዝ ለረዥም ዓመታት ውጤታማ ዝግጅቶችን አካሂዷል። ከዚህም በተጨማሪ በሜሪላንድ ክፍለ ሀገር ውስጥ በሚገኘው የሞንትጎመሪ አውራጃ ውስጥ የአድዋ ድል በአዋጅ እንዲዘክርና እንዲታሰብ አስደርጓል። ድርጅታችን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ተቋም የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ይከታተላል። በዚህም መሠረት ካለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል አንስቶ በተለየ ሁኔታ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች ውስጥ እየደረሰ ያለው ማንነትንና ሐይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በእጅጉ አሳዝኖናል አስቆጥቶናልም። የተሳሳተ የፖለቲካ አስተሳሰብ የወለደው የጭካኔ ድርጊት የዜጎች ፍጅትን፣ ንብረት ውድመትን፣ ዘረፋን፣ የአብያተ ክርስትያናትን መቃጠል በማስከተሉ በእጅጉ አሳዝኖናል፣ አስቆጥቶናልም። ክርስቲያንና ሙስሊም ተከባብሮና ተፋቅሮ በሚኖርባት አገር ውስጥ በማናቸውም ቤተ እምነት ላይ የሚደርስ ጥቃት እጅግ ከባድ ወንጀል በመሆኑ በዝምታ መታለፍ እንደሌለበት እናምናለን።

ኢትዮጵያዊያን በፈለጉትና በመረጡት ቦታ የመኖርና የመሥራት ህጋዊ መብታቸው ተጥሶ ለስደተኞች ሊደረግላቸው የሚገባ ሰብዓዊ እንክብካቤ አንኳ ተነፍጓቸው፤ አያት ቅድመ አያቶቻቸው ተወልደው ባደጉበትና እትብታቸው በተቀበረበት ቦታ እጅግ በሚሰቀጥጥ ሁኔታ አማራና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ በመሆናቸው ብቻ ተለይተው ሲታረዱና አካላቸው ሲቆራረጥ፣ አይናቸው ተጎልጉሎ ሲወጣ፣ እርጉዝ ሴቶች ማህጸናቸው በጩቤ ተዘርግፎ ጽንሳቸው ሲጨነግፍና አስከሬናቸው ተቆራርጦ ሲጣል ከመመልከት የከፋ መከራ በዚህ ዓለም ላይ ይመጣል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ይህ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ ዘግናኝ ድርጊት አገራችን ውስጥ በመፈዘሙ ከልብ አዝነናል። ይህ ሁሉ ጭፍጨፋና ውድመት ሲካሄድ የመንግሥት አካላት የሆኑት መከላከያ ሠራዊት፣ ፖሊሶችና “ልዩ ኃይሎች” እንዲሁም የአስተዳደር ሠራተኞች፣ እልቂቱን ማስቆምና የዜጎችን ህይወት መታደግ ሲገባቸው የጥፋቱ ተባባሪ ሆነው መገኘታቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ተለቀዋል። የአማራ ብሔረሰብ አባላትና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ተከታዮች ስም ዝርዝርና የሚኖሩበት የቤት ቁጥር ተለይቶ ቤታቸው ውስጥ እያሉ በመንግስት እይታ ሥር እንዲጨፈጨፉ ተደርገዋል። ግድያው የተፈጸመው ቤታቸው ውስጥ መሆኑ ግድያው በዕቅድ የተመራና የአካባቢው ሹመኞች እጅ እንዳለበት የሚያረጋግጥ ነው። በተግባር ከደረሰው አኳያ በጥቂቱ ጠቀስነው እንጅ ዘርና ሐይማኖት ላይ ያተኮረ እጅግ የሚዘገንና የሚሰቀጥጥ የጭካኔና የጥላቻ ድርጊት ተፈጽሟል።

በኢትዮጵያ የወንጀለኞች መቅጫ ሕግና በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድንጋጌዎች መሠረት እየደረሰ ላላው የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈለግለት እንጠይቃለን። መንግሥት ከፈለገ ሮጦ የመድረስ አቅሙ እንደ አውሎ ነፋስ ፈጣን መሆኑን በሶማሌ ክልል፣ በአማራ ክልልና በቅርቡም በዎላይታ ዞን ከተወሰዱት እርምጃዎች ለመረዳት ይቻላል። ሆኖም በቡራዩ፣ በሻሸመኔ፣ ኮፈሌ፣ ዝዋይ፣ በባሌ፣ዶዶላ፣ሀረር፣ድሬዳዋ፣ መተከልና ሌሎችም ቦታዎች ይህ ፍጥነት አለመታየቱ ያሳዝናል። ይዋል ይደር ሊባል የማይገባውና አሁኑኑ ሥራ ላይ መዋል ያለበት ኦሮሚያና ሌሎች ክልሎች ውስጥ በአማራዎችና በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ላይ ጀኖሳይድ የሚፈጽመውን እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያለውን ወንጀለኛ የቄሮ መንጋ በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ ማቅረብ ነው። የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) የማስቆምና ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ እንዲሁም የአገሪቷን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነትን መንግሥት በአፋጣኝ እንዲወጣ እያሳሰብን፤ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር እንደ አንድ ተቆርቋሪና ጉዳዩ እንደሚመለከተው ተቋም ከዚህ በታች የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች ያቀርባል፤

1. የወንጀል ድርጊትን መደበቅ የህዝብን አመኔታ ሰለሚያጠፋ ቡራዩ፣ ሻሸመኔ፣ ኮፈሌ፣ ዝዋይ፣ ባሌ፣ዶዶላ፣ ሀረር፣ ድሬዳዋ፣ መተከልና ሌሎችም ቦታዎች ውስጥ የተፈጸመው ተራ ወንጀል ሳይሆን የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ስለሆነ በትክክለኛው የወንጀሉ ስም ጀኖሳይድ ወይም የዘር ማጥፋት ተብሎ አንዲገለጽ እንጠይቃለን።

2. በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት በሚገኙ በዜና ማሰራጫዎችና በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ የጥላቻና “የግደለውና የእረደው” አዋጅ አውጀው፣ የጥቂት ወጣቶችን አዕምሮ በጥላቻ መርዘው ጀኖሳይድ ያደረሱ ቡድኖች፣ ግለሰቦች፣ ድጋፍ ሰጪዎችና እንዲሁም ሆን ብለው የጥፋቱን ሀሳብ ያፈለቁና የተባበሯቸው የመንግሥት አካላት ሁሉ ማንነታቸው ተጣርቶ ለፍርድ ማቅረብ የመንግስት ኃላፊነትና የስራ ድርሻ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

3. የቤተሰብ አባላት ለተገደሉባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሁም ቤታቸው፣ ሱቃቸው፣ መኪናቸው፣ መጋዘናቸውና ልዩ ልዩ ዓይነት ንብረቶቻቸው ለወደመባቸውና ለተዘረፋባቸው ዜጎች በአስቸኳይ ካሳ የመስጠትና ሕይወታቸው እንደገና እንዲቀጥል የማድረግ ኃላፊነት የመንግሥት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

4. በተደራጀ የመንጋ ጥቃት የፈረሱ ሃውልቶች ተመልሰው የነበሩበት ቦታ ላይ እንዲተከሉ አንዲሁም የተቃጠሉና የፈረሱ ቤተክርስቲያኖች፣ መስጊዶችና ሌሎችም የማህበረተሰብ መገልገያዎች ተመልሰው እንዲገነቡ እየጠየቅን በዚህም የመልሶ መገንባት ሥራ ድርጅታችንም ሆነ ሕዝብ ተሳታፊ እንዲሆን እድሉ እንዲመቻች እንጠይቃለን።

5. ቤተክርስቲያኖች፣ መስጊዶች፣ ሀውልቶች፣ ቅርሶችና የተለያዩ የማሕበረሰብ ንብረቶች ላይ ጥቃትና ዝርፊያ እንዳይደርስ መንግሥት ልዩ ጥበቃ እንዲያደርግ እየጠየቅን ሕዝቡም ቅርሶችንና የማሕበረሰብ መገልገያዎን በመጠበቅና በመንከባከብ ረገድ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ መስራት እንዳለበት እናሳስባለን። እኛም ለዚህ ተግባር የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን።

6. ከሁሉም በላይ ለዚህ ሁሉ ጥፋት ምንጭ የሆነውን የውሽት የታሪክ ትርክትና በቅጥፈት የተበከለ የፖለቲካ መስመርን ማምከን በተመለከተ መንግሥት ሳያሰልስ ለሁሉም ዜጎች የሚሰጥ የሰውን ልጅ ክብርና የአብሮነትን ጥቅም የሚያስገነዝብ አገር አቀፍ ሰፊ የተሀድሶ ዘመቻ እንዲያደረግ አጠንክረን እንጠይቃለን። መሠረተ ቢስ በሆነ የሀሰት የታሪክ አስተሳሰብና የጥላቻ ፍልስፍና ላይ ተመርዞ ያደገ ወጣት ከማጥፋት አይድንምና አስተሳሰቡን ለማስተካከል መንግስትና ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የሥራ ድርሻና ኃላፊነት መሆኑን እየጠቆምን እኛም አቅማችን በሚፈቅደው መጠን ለመተባበር ዝግጁ መሆናችንን አንገልጻለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር በሰሜን አሜሪካ

ግልባጭ፣
ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት
ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
ለኢትዮጵያ ባሕል ሚኒስቴር
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ
ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ስቴት ዲፓርትመንት)
አፍሪካ ዋች
ጀኖሳይድ ዋች
የአውሮፓ ኮሚሽን
ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩፕ
ለአምነሲት ኢንተርናሽናል
ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ (WCC)
ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
ለኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ዋሽንግተን ዲሲ

የ124ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ሊከበር  ነው። -EHSNA

የኢትዮጵያውያን ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ

የ124ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ሲያበስር በደስታ ነዉ:: (The 124th Victory of the Battle of Adwa Celebration in Silver Spring)

እጅግ ታላቅና አኩሪ የሆነው የአድዋ ድል በዓላችን በኢትዮጵያውያን ዉርስና ቅርስ ማህበረሰብ በዲስ አካባቢ ሲከበር ለዘጠነኛ ጊዜ ሲሆን በዕለቱ የሚደረግገ ው የአድዋ ድል በዓል በዲሲ ዙሪያ በሚኖሩ የኢትዮጵያውያንና ሌሎች የማህበረሰብ አባላት ፤ የሞንትጎመሪ ካዉንስል አመራሮች ፤ ታዋቂ የክብር እንግዶች በሚገኙበት በንግግር ፤ በስነ ግጥም ፤ በአጭር ተዉኔት  የመሳሰሉትን አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በማቅረብ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል::

በተለይም በዚህ ዓመት ታዋቂዉ የታሪክ መምህርና ፀሐፊ የሆኑትን አቶ ታዬ ቦጋለ አረጋ ከኢትዮጵያ በመጋበዝ የአድዋ ድል በጥልቀት የሚዳስስ ንግግር ያቀርባሉ። ከዚህም በተጨማሪ ታዋቂዉ የጣይቱ ማዕከል ጋር በመተባበር የዳግማዊ አፄ ምኒልክንና የእቴጌ ጣይቱን  የጦርነቱን የአመራር ስልት የሚያሳይ አጭር ተውኔት ስለሚቀርብ በመዝናናት ታሪክዎን ያድሳሉ ::

ዝግጅቱ የሚደረገው ዳዉንታውን በሚገኘው የሲልቨር ስፕሪንግ የሲቪክ ማዕከል (1 Veterans Place, Silver Spring, MD, 20910) ቅዳሜ፣ የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (Saturday, February 29, 2020)  ከቀትር 1:00 አንስቶ እስከ 6:00 ፒ. ኤም ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን የበለጠ መረጃ ለማግኘት በኢሜይል info@ehsna.org  ወይም በስልክ  ቁጥር 615-412-9094 መጠቀም  የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ዝግጅት ላይ በመገኘት ታሪክዎንና ባህልዎን እንዲያከብሩ የኢትዮጵያውያን ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ ከውዲሁ በአክብሮት ጋብዝዎታል።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 

https://youtu.be/oTcRJC8WFu0?t=77

“MARCH 2017 AS ADWA VICTORY MONTH” Montgomery County, MD – EHSNA PR

For immediate release: 3/3/17

Ethiopian Heritage Society in North America (EHSNA) is proud to announce that on this 121st Anniversary of the Victory of the Battle of Adwa, the Honorable Isiah Leggett, Executive, Montgomery County, MD has proclaimed:

“MARCH 2017 AS ADWA VICTORY MONTH”

EHSNA believes this may be the Second time such an honor has ever been bestowed on this historical Victory. This has happened despite the apparent presence of documented facts that, the great victory Ethiopia achieved against the invading Italian forces, with outstanding leadership of Emperor Menilik II and his right arm Queen Taitu, was a major world historical event not only to Ethiopians but to black people worldwide. We hope this recognition by the Executive of Montgomery County will set an example for others to follow.

Finally, in behalf of EHSNA and those millions Ethiopians who are proud admirers of the Victory of the Battle of Adwa, we express our heartfelt gratitude to the Honorable Isiah Leggett for this historical proclamation he passed. We encourage the Ethiopian community to join EHSNA and celebrate the 121st Anniversary of the Victory of Adwa, on March 4, ( 12 – 4:30PM),where we will take the opportunity to formally thank and recognize Mr. Leggett for his support.

The event will be held at the Civic Building, One Veteran Place, Silver Spring, Maryland, 20910.

For more information, please visit: www.ehsna.org

PUBLIC MESSAGE WHAT IS MEANING OF “THE VICTORY OF THE BATTLE OF ADWA”

Ethiopian Heritage Society of North America (EHSNA) is gathering message from the public about The Victory of the Battle of Adwa. The message could be audio, video or written and it should be no more than 5 minutes long. Send your message to adwa@EHSNA.org Or leave a voice mail 202-596-1964.

Read morePUBLIC MESSAGE WHAT IS MEANING OF “THE VICTORY OF THE BATTLE OF ADWA”

REMEMBERING EMPEROR MENELIK II ON THE 100TH YEARS ANNIVERSARY OF HIS DEATH!

It has been a 100 years since the death of Emperor Menelik II, who is highly considered as a prudent leader since he hadn’t trapped with the other African leaders to give the imperial powers to powerful European nations instead he was determined, mobilized every Ethiopians to fight and defeat the Italian foreign aggressor at the 1896 Battle of Adwa followed by a disputed treaty knows as Wechale. In addition, he was widely known for introducing the country to modernization.

Teenage Ethiopian Americans Bring Their Parents’ Music to Life – BY SAM HARNETT

Full-Band.Noam_

Members of the Young Ethio Jazz Band (Photo: Noam Eshel)

It’s a truth universally acknowledged that kids hate their parents’ music, or at least do their best to ignore it. Garage bands don’t borrow CDs from their parents so they can practice disco covers.

Okay, maybe, but only in some kind of ironic hipster way.

Well there’s nothing ironic about the music being played in this suburban garage near Oakland, California. The Young Ethio Jazz Band are teenagers who rock out with their parents’ music.

The band played its first gig in San Francisco last winter. Now it is slated to open for another act at Yoshi’s, a famous jazz club in San Francisco, and then it plays in the Ethiopian Heritage Festival at Georgetown University in Washington, DC.

All of the kids are second generation Ethiopians between 11 and 16-years-old. Before they started playing together a year and a half ago, most of them had the stereotypical reaction to their parents’ music.

“In the very beginning I was really confused about the music,” says Yohanas Abanew, who plays keyboard in the band. “I just said ‘well this doesn’t really sound like music that I would really want to play.’”

Then he started practicing an Ethio-jazz song in his high school band. “It really woke me up,” he says, “this is my culture, and I really need to learn this music.”

Yonathan Wolday had a similar revelation. He’s a tall, lanky 16-year-old who plays trumpet. Wolday is wearing a gray sweatshirt with a picture of a diamond and the letters “DMND.” A pair of white ear phones hang out from his collar and onto his chest.

His parents are from Ethiopia, and the songs they listen to are in Amharic, the official language in Ethiopia. Wolday doesn’t understand it well, and that initially turned him off from the music. He didn’t really start listening to the songs until he began playing in the band.

Even now, it’s hard to believe that he’s channeling the music of his parents’ generation. Whenever the band stops practicing, you can hear simple rap bass lines pulsating out from his dangling ear buds.

Vibraphonist Mulatu Astatke gave birth to Ethio-jazz in the early 70s. He was the first African student to attend the Berklee College of Music in Boston. There he fused Western jazz with Latin rhythms and traditional Ethiopian scales.

If you watched the movie “Broken Flowers” you may have one of his songs stuck in your head. The score features several Astatke compositions, including this one, Yekeramo Sew.


Mulatu Astatke and Ethio-jazz have had a bit of a resurgence in the US since “Broken Flowers” came out in 2005. Still, it’s hard to find sheet music and transcribed parts for many Ethio-jazz songs.

So, instead of relying on charts, the Young Ethio Jazz Band is learning the music the old fashion way — by ear. Their accuracy is astonishing. At moments they sound almost identical to Astatke’s recordings.

Sirak Tegbaru brought the band together. He invited the kids to practice in his garage after after hearing them play at a nearby church. Even he is impressed with how well the kids have internalized the music.

“These kids really just want to play it the way it’s been played,” Tegbaru says. Sometimes he has to encourage them to branch out—play some different scales, improvise their own solos over the chord changes. Make the kids break the rules.

Tegbaru left Ethiopia in 1979 when he was 16. He loved playing music, but his parents said it wasn’t practical. They pressured him to study medicine, and sent him abroad to Prague. Tegbaru still plays music, but he doesn’t have anything to do with medicine. He sells State Farm insurance during the week. On the weekend, he leads the band.

“I feel like I am reborn again through these kids,” he says. The kids they glow when they play this song. They smile on their face. They’re happy and moving around. That means they really have that feeling. They’re playing from the bottom of the heart. And that’s, that’s music.”

The band has until July 26th to practice for the Ethiopian Heritage Festival at Georgetown University. It’s their biggest gig yet.

I ask the kids if they’re nervous. At first they say no. Then Tegbaru reminds them that as many as 10,000 people could attend the festival.

Semon Yacob who plays keyboard says in very matter-of-fact voice, “you can’t imagine how excited I am.”