የ124ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ሊከበር  ነው። -EHSNA

የኢትዮጵያውያን ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ

የ124ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ሲያበስር በደስታ ነዉ:: (The 124th Victory of the Battle of Adwa Celebration in Silver Spring)

እጅግ ታላቅና አኩሪ የሆነው የአድዋ ድል በዓላችን በኢትዮጵያውያን ዉርስና ቅርስ ማህበረሰብ በዲስ አካባቢ ሲከበር ለዘጠነኛ ጊዜ ሲሆን በዕለቱ የሚደረግገ ው የአድዋ ድል በዓል በዲሲ ዙሪያ በሚኖሩ የኢትዮጵያውያንና ሌሎች የማህበረሰብ አባላት ፤ የሞንትጎመሪ ካዉንስል አመራሮች ፤ ታዋቂ የክብር እንግዶች በሚገኙበት በንግግር ፤ በስነ ግጥም ፤ በአጭር ተዉኔት  የመሳሰሉትን አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በማቅረብ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል::

በተለይም በዚህ ዓመት ታዋቂዉ የታሪክ መምህርና ፀሐፊ የሆኑትን አቶ ታዬ ቦጋለ አረጋ ከኢትዮጵያ በመጋበዝ የአድዋ ድል በጥልቀት የሚዳስስ ንግግር ያቀርባሉ። ከዚህም በተጨማሪ ታዋቂዉ የጣይቱ ማዕከል ጋር በመተባበር የዳግማዊ አፄ ምኒልክንና የእቴጌ ጣይቱን  የጦርነቱን የአመራር ስልት የሚያሳይ አጭር ተውኔት ስለሚቀርብ በመዝናናት ታሪክዎን ያድሳሉ ::

ዝግጅቱ የሚደረገው ዳዉንታውን በሚገኘው የሲልቨር ስፕሪንግ የሲቪክ ማዕከል (1 Veterans Place, Silver Spring, MD, 20910) ቅዳሜ፣ የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (Saturday, February 29, 2020)  ከቀትር 1:00 አንስቶ እስከ 6:00 ፒ. ኤም ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን የበለጠ መረጃ ለማግኘት በኢሜይል info@ehsna.org  ወይም በስልክ  ቁጥር 615-412-9094 መጠቀም  የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ዝግጅት ላይ በመገኘት ታሪክዎንና ባህልዎን እንዲያከብሩ የኢትዮጵያውያን ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ ከውዲሁ በአክብሮት ጋብዝዎታል።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 

https://youtu.be/oTcRJC8WFu0?t=77