የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበረሰብ ቦርድ የብፁዕ አቡነ መልከጻዲቅን ዜና እረፍት በማውሳት ሀዘኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበረሰብ ቦርድ ታሕሳስ ሶስት ቀን ባደረገው ልዩ ስብሰባ ስለ መቶ ሃያ አምስተኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ተጋባዦች ዝርዝር ከተነጋገረ በሁዋላ፤ በቪድዮ አስተያየት ስለሚያቀርቡት የተለያዩ የህብረተሰብ ወገኖች የወጣውን እቅድ አጽድቆ ለእለቱን የተያዘውን የስብሰባ አጅንዳ ጨርሱዋል። ከዚህም በማስከተል ስለብፁዕ አቡነ መልከጻዲቅ እረፍት በስብሰባው ላይ በማውሳት ቦርዱ የተሰማውን ሀዘን በውይይት ገልጹዋል። እንደሚታወቀው በተከታታይ ሶስት ታላላቅ ሰዎች፤ አቶ ለማጉያና ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ ከሕብረተሰቡ መለየታቸው ሀዘኑ ለጎዳችው ወገኖቻችን በሙሉ መጽናናትን እየተመኘን ስለ ብፁእነታችው የህይወት ታሪክ በወገኖቻቸው የተዘጋጀውን ቪድዮ እንድትመለከቱት ከዚህ ጋራ ከታች አቅርበናል።

ለይኩን ካሣሁን
ሕዝብ ግንኙነት
pr@eshna.org