የመቶ ሃያ አምስተኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ልዑል ዶክተር አስፋወሰን አስራተ ካሣ በክብር እንግድነት እንደሚገኙ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ ቦርድ ሕዳር ሃያ ስድስት ቀን ባደረገው ስብሰባ ለመቶ ሃያ አምስተኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ልዑል ዶክተር አስፋወሰን አስራተ ካሣ በክብር እንግድነት እንዲገኙ ውሳኔ በሙሉ ድምጽ ያሳለፈ ከመሆኑም በላይ፤ ክቡርነታችው የአጼ ሚኒሊክ አጎት የስመ ጥሩው የራስ ዳርጌ የልጅ ልጅ በመሆናቸው፤ ለበዓሉ ለመላው አያቶቻችን ለምናደርገው ታላቅ የምስጋናና የክብር ቀን የክቡርነታችው መገኘት በዓሉን ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠውም ተወስቱዋል። በማግስቱም ሕዳር ሃያ ሰባት ቀን ልዑል ዶክተር አስፋወሰን በክብር እንግድነት በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ተጠይቀው፤ እሳቸውም ጥሪውን ተቀብለው መልካም ፈቃደኛ መሆናቸውን አበክረው ገልጸዋል። ቦርዱ በዓሉ የሚከበረው ማርች ስድስት /የካቲት ሃያ ሰባት/ መሆኑንም በዚሁ እለት ባደረገው ስብሰባ ውስኑዋል፡፡ በዚሁም ስብሰባ ወላጆች ልጆቻችውን የአገር ስሜታችውን እንዲገልጹ በአድዋ ድል ላይ ከሶስት ደቂቃ ያልበለጠ የንግግር ወይም ተውኔታዊ ገለጻ ቪድዮ ቀርጸው በተለያየ መድረክ እንዲልኩልን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተወያይተዋል። ወላጆች ለቦርድ አባላት ወይም በኢሜል ለ pr@ehsna.org ወይም ፌስ ቡካችን ላይ facebook.com/ehsna ቢልኩ የምናመሰግን መሆናችንን ከወዲሁ እንገልጻለን።

ለይኩን ካሣሁን
ሕዝብ ግንኙነት

c