የመቶ ሃያ አምስተኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለየ ሁኔታ እንደሚከበር መሀበሩ ዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ።

የ125ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በአማራጭ ዜና ማሰራጫ ሊከበር ነው። ለዚህ ዝግጅት ጽሁፍ አቅራቢዎችን ለመጋበዝ የመሀበሩ ቦርድ አባላት ዝግጅት ላይ መሆናቸውም ይገመታል። ይህ ታላቅ የጥቁር ሕዝቦች ድል በወቅቱ የኮሮና ተስቦ በሽታ ምክንያት እንደታሰበው በከፍተኛ ሁኔታ በምልዓተ ሕዝብ ማክበር ባይቻልም፤ በአማራጭ ዜና አገልግሎት በዓሉን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን የመሀበሩ አመራር አባላት እየተነጋገሩበት መሆኑም ታውቁዋል።