ክቡር አምባሳደር ዘውዴ ረታ አጭር የሕይወት ታሪክ

zewdeክቡር አምባሳደር ዘውዴ ረታ ... ሐምሌ 27 ቀን 2012 የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበረሰብ ባደረገላቸው ጥሪ መሠረት በዕለቱ የክብር እንግዳ በመሆን ተገኝተው ለዝግጅታቸን ልዩ ድምቀት ክብር ሰጥተውት ነበር። በዚህም ጊዜ የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የተሰኘውን የመጨረሻ ያሳተሙትን መጽሃፋቸውን በዝግጅታችን ላይ ለተገኙት ታዳሚዎች አቅርበው ፊርማቸውን አኑረዋል። የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር በሰሜን አሜሪካ የአማባሳደር ዘውዴ ረታን ህልፈት በማስመልከት ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐዘኑን እየገለጸ እግዚያብሔር መጽናናትን እንዲሰጥ ይመኛል።

 

የክቡር አምባሳደር ዘውዴ ረታ አጭር የሕይወት ታሪክ

 

አምባሳደር ዘውዴ ረታ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ነሐሴ 7 ቀን 1927 .. አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተወለዱ

1933 እስከ 1945 .. ድረስ ቀድሞ ቀድሞ ደጃዝማች ገብረ ማርያም ይባል በነበረውና ኋላ ሊሴ ገብረማርያም ተብሎ በተሰየመው የፈረንሣይ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውንና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አከናውነዋል፡፡

1945 እስከ 1948 . በጋዜጣና ማስታወቂያ መሥሪያ ቤት የቤተመንግሥት ዜና ጋዜጠኛና በራዲዮ ዜና አቅራቢነት አገልግለዋል

1948 እስከ 1952 . በፓሪስ የጋዜጠኝነት ሞያ በማጥናት በዲፕሎማ ተመረቁ

1952 እስከ 1954 . የኢትዮጵያ ድምፅ ጋዜጣና የመነን መጽሔት ዲሬክተር

1954 እስከ 1955 . የኢትዮጵያ ሬዲዮ የብሔራዊ ፕሮግራም ዲሬክተር

1955 እስከ 1958 . የኢትዮጵያ ወሬ ምንጭ ዋና ዲሬክተር

1958 እስከ 1960 . የማስታወቂያ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር

1960 እስከ 1962 . የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ

1956 እስከ 1962 . የፓን አፍሪካ ኒውስ ኤጀንሲ ማኅበር ፕሬዚዳንት

1962 እስከ 1967 . ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዛውረው

 

በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሚኒስትር ካውንስር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር /ሚኒስቴር

በሮም እና በቱኒዚያ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል

 

በጠቅላላው በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የሀያ ሁለት ዓመታት አገልግሎት ካበረከቱ በኋላ በወታደራዊው አስተዳደር ዘመን 1967 . ጀምሮ ስደተኛ ሆነው በአውሮፓ በቆዩበት ዘመን በሮም የኢንተርናሽናል ድርጅት ውስጥ (IFAD) ለአሥራ ሦስት ዓመታት በፕሮቶኮልና በመንግሥታት ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡

1959 . ጋብቻቸውን መሥርተው ከሕግ ባለቤታቸው ከወይዘሮ ገሊላ ተፈራ ጋር ሦስት ልጆችን አፍርተዋ። ከንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የምኒልክ የመኮንን ደረጃና የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ አዛዥ መኮንን ኒሻን ተሸልመዋል፡፡ እንዲሁም ከአፍሪካ ከእስያና ከአውሮፓ በድምሩ ከሀያ ሁለት አገሮች የታላቅ መኮንን ደረጃ ኒሻኖች ተሸልመዋል፡፡ ከዚህ ቀደም 1945 እና 1946 . አራት ቲያትሮችን አዘጋጅተዋል። 1992 . የኤርትራ ጉዳይ፣ 1997 . ተፈሪ መኮንን በቅርቡም የቀድሞ ኃይለሥላሴ መንግሥት የተሰኙትን መጻሕፍቶች ለንባብ አብቅተዋል፡